ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን MBA & BA ዲግሪ ፕሮግራሞችን ላለፉት 9 አመታት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
አሁን ደግሞ አድማሱን በማስፋት ከAmerican Academy of Financial Management ጋር በመተባበር Certified Credit Analyst ላይ ለአንድ ሳምንት (ከነሐሴ 27 እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ.ም) የሚቆይ የአጭር ጊዜ ስልጠና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ከሌሎች ባንኮች እና ተጔዳኝ የሙያ ዘርፎች ለመጡ ከፍተኛ የሂሳብና ክሬዲት ባለሙያዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል ፡፡
ተቋሙ ከሚሰጠው መደበኛ ትምህርት በተጔዳኝ ከአሁን በፊት Stock Market (የካፒታል ገበያ) ላይ ተመሳሳይ ስልጠና የሰጠ መሆኑን አቶ አቤቱ መላኩ የዩንቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዚዳንት ጨምረው ገልጸዋል፡፡