የምስራች!

ከፍተኛ የትምህርት ተቁዋማችን ማለትም Western University College affiliated Lincoln University, California በመንግስት የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 89% የሚሆኑት የመውጫ ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት ማለፋቸውን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቁዋማት ተማሪዎች ያገኙት ውጤት 17% ብቻ ነው ቢባልም የኛ ተማሪዎች ግን በተለየ ሁኔታ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በቅተዋል፡፡ ለተማሪዎቻችን የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ዋናው ምክንያት የተቁዋማችን የትምህርት አሰጣጥ ስርአት የተዋቀረበት እና በዋናነት የሚያተኩረው የተማሪዎቻችን ክሂሎት በመገንባት ላይ በመሆኑ ነው፡፡

ተማሪዎቻችን ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ሲመረቁ ሰርቲፊኬት ብቻ ይዘው እንዲወጡ ሳይሆን የሚሰጣቸው ሰርቲፊኬት በአለም አቀፍ ደርጃ ለስራ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ክሂሎት መያዛቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር እንዲሆን ብዙ የተደከመበት መሆኑ ነው፡፡ ስለሆነም በተገኘው ውጤት ደስ ያለኝ ብሆንም ብዙም አላስገረመኝም፡፡ ለተገኘው ድንቅ ውጤት ምክንያቱ የተማሪዎቻችን ታታሪነት የመምህራናኖች ብርቱ የስራ ትጋት የተቀናጀበት በመሆኑ ነው መልካም ፍሬ እንደሚያስገኝም ለአፍታም አልተጠራጠርኩም፡፡ ማንም ሊስተው የማይገባዉ  ሃቅ የአንድን አገር እጣ ፈንታ የሚወስነው የትምህርት ስርአቱ አወቃቀር መሆኑን ነው፡፡

በጥራት ላይ የተመሰረተ ትምህርት ለወገኔ !!”

 

አቤቱ መላኩ

ፕሬዝዳንት እና ተባባሪ ፕሮፌሰር

ዌስተርንዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ, አዲስ አበባ

ከሊንከን ዩኒቨርሲቲ ካሊፎርኒያ ጋር በመተባበር!